የከሰአት የስልጠናዉ መርኃ ግብር

ቀን ፡-24/03/2013
ቦታ፡- አዳማ ራስ ሆቴል

ከሰአት በቀጠለው የስልጠና መርኃ ግብር በውድድር እና ከውድድር ጊዜ ወጪ አትሌቶች የጸረ-አበረታች ቅመም ምርመራ መምረጥና ማሳወቅ ሂደትን (Athlete Notification and selection process , In competion and out of competion ) በሚመለከት በተግባር የተደገፈ ስልጠና በአቶ ቢኒያም ጌታቸው ሲኒየር የዶፒንግ ቁጥጥር ባለሙያ (DCO) አማካኝነት ለሰልጣኞች ቀርቧል።

በስልጠናው አንድ አትሌት በምርመራ ወቅት የሚኖሩት መብትና ግዴታዎች እንዲሁም የዶፒንግ ቁጥጥር ባለሙያው ( Doping conterol officer ) በምርመራ ወቅት የሚገጥሙትን ችግሮች እንዴትና በምን መንገድ ማስተናገድ እንዳለበት የሚያሳይ ስልጠና ተሰጥቷል።
በተጨማሪም የላብራቶሪ ቴክኒሻን ባለሙያ በሆኑት በአቶ ጌታሁን ጸጋዬ በደም ናሙና አሰባሰብ ሂደት ወቅት (collection of Blood Samples) ልንከተላቸው የሚገቡ ቅደም ተከተሎች ዙሪያ በተግባር የተደገፈ ስልጠና ከባለሙያዎች ጋር በመሆን ለሰልጣኞች ሰጥተዋል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *