የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከክልሎች/ የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ለማርሻል አርት ስፖርት እና ለጂምናስቲክ ፌድሬሽን ኃላፊዎች እና አሰልጣኞች፣ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ እዲሁም በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (supplements) ዙሪያ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና በአዳማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
አዳማ ከተማ፤ አርብ ህዳር 24 /2014 ዓ.ም ፡- በክልልና ከተማ አሰተዳደር ስር ለሚገኙ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚወዳደሩ ለማርሻል አርትስ ስፖርትና ለጂምናስቲክ ፌድሬሽን አመራሮችና አሰልጣኞች ከህዳር 24/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት በአዳማ ከተማ ኤፍታህ ኢንተርናሽናል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጨምሮ ስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (supplements) ዙሪያ በአዳማ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት እና የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋነታዬ ገዘኽኝ የስልጠና መድረኩ የስፖርቱ ማህበረሰቡ የስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮችን፣ጉዳቱን፣ሕግና ደንብን እዲሁም በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (supplements) በአግባቡ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና ሌሎችንም እንዲያሳውቁ እድል እንደሚፈጥርም ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እስካሁን ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀው በቀጣይም በየደረጃው ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የተለያዩ የስልጠናና የውይይት መድረኮች እንዲሁም የህዝብ ንቅናቄ ተግባራት እንዲከናወኑ በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ ለስፖርቱ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለማጎልበት ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዛሬው የስልጠና ውሎ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግና በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶች እዲሁም በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (supplements) ዙሪያ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ከ85 በላይ ለሚሆኑ ከአዲስ አበባ፣ከኦሮሚያ ፣ከደቡብና ከሲዳማ በሔራዊ ክክልሎች ለተውጣቱ የማርሻል አርት ስፖርት እና የጂምናስቲክ ፌድሬሽን ኃላፊዎችና አሰልጣኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ሥልጠናውን የተከታተሉት ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን በተዘጋጀው የፀረ-ዶፒንግ ረቂቅ የሕግ ማዕቅፎች ዙሪያ ገለፃ እደሚደረግ ታውቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *