የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNECO) የፀረ-ዶፒንግ ዲፓርትመንት የስራ ኃላፊዎች እና የአገራችን National Compliance Program Platform አባላት የጋራ ውይይት ተካሂዷል።

አገራችን ኢትዮጵያ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የአለም አቀፉን የፀረ-ዶፒንግ ስምምነት (Anti-Doping Convention) ተቀብላ በአዋጅ ቁጥር 554/1999 አፅድቃለች። ይሁን እንጅ ላለፉት ረዥም ጊዜያት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ እዚህ ግባ የሚባል ስራ ሳይሰራ ቆይቷል።

ስለሆነም የኢፌዲሪ መንግስት ይህን በመገንዘብ ላለፉት ሶስት ዓመታት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲፈፀም ያደረገ ሲሆን በአጭር ጊዜም ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። የUNESCO Compliance ፕሮግራምንም ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳካት ተችሏል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNECO) የፀረ-ዶፒንግ ዲፓርትመንት ከኢትዮጵያ National Compliance Program Platform ጥር 17/2013 ዓ.ም የጋራ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። ከላይ እንደተገለፀው በአገራችን አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት እየተካሄዱ ያሉ እንቅስቃሴዎች እና የተገኙ ውጤቶች በውይይት መድረኩ ላይ በዝርዝር ቀርበዋል።

ከህግ ማዕቀፎች ዝግጅትና ትግበራ፣ ከባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣ ለስራው በቂ ኃብት ከመመደብ እና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በተቋሙ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም በቂ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ይህንንም መነሻ በማድረግ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNECO) የኢንተርናሽናል የፀረ-ዶፒንግ ሴክሬታሪያት Mr. Marcellin Dally የአገራችን አፈፃፀም አመርቂ መሆኑን ገልፀው ተሞክሮውን ለሌሎች አገሮችም ለማስፋት እንዲቻል አስፈላጊ ሰነዶች ለድርጅቱ እንዲላኩ አሳስበዋል።

የአገራችን አጠቃላይ አፈፃፀም 95.2 % ሲሆን ይህም በቀጣይ እ.ኤ.አ የካቲት 04-06/2021 ሴኔጋል ዳካር ላይ በሚካሄደው የድርጅቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ እንደሚፀድቅ አሳውቀዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽንን ጨምሮ የአገራችን የNational Compliance Program Platform አባላት የሆኑት የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የፌዴራል መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የመሳሰሉት ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች ተሳትፈዋል።

No photo description available. 

 

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *