ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ የመፍጠር የOutreaching ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ ፡፡
 
ከጥር 23-28 /2015 ዓ.ም በአሰላ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ከተለያዩ ክልልሎች እና ክለባት ለተገኙ ታዳጊ ስፖርተኞች ፣ የስፖርት ባለሞያዎች ፣ የስፖርቱ ተሳታፊዎች እንዲሁም የስፖርቱ ማህበረሰብ በፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ የመፍጠር የOutreaching ፕሮግራም በስፋት በማካሄድ በዛሬ ዕለት ተጠናቋል፡፡
 
በፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤና ንቅናቄ ፕሮግራሙ ላይ ሰፊ ስራዎችን መስራት የተቻለ ሲሆን በዚህም ስፖርተኞችን በማዝናናት ራሳቸውን ከስፖርት አበረታች ቅመሞች መጠበቅ የሚችሉበትን ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡
 
በቀጣይም ይህ የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና የንቅናቄ ፕሮግራም ከጥር 29 እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም በሚካሄደው 4ኛው የኦሮሚያ ከ16 ዓመት በታች እና ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ውድድር ላይ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ዶፒንግን በጋራ እንከላከል!!!
 
 
 
 
 
 
 
 
May be an image of 2 people and screen

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *