ጽ/ቤታችን /ETH-NAD0/ ከሌሎች ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም የኢፌድሪ ሰፖርት ኮሚሽን በተገኘበት ውይይት አደረገ ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከኢትዮጲያ ወጣቶች አካዳሚ እና ከአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከል ጋር በመሆን የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር እና የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ በተገኙበት ዛሬ ጥር /20/2013 ዓ.ም በኮሚሽኑ የመሰብስቢያ አዳራሽ ውይይቱን አድርጓል፡፡
በሪፖርቱም የተቋሙን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተጠናከረ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት ከመደገፍ አንጻርም፣ትምህርት፣ ስልጠና እና የህዝብ ንቅናቄ በሚመለከት ፣ምርመራና ቁጥጥር ስራውን በሚመለከት ፣ቅንጅታዊ አሰራርና አለም አቀፍ ግንኙነቱን ማጠናከርን በሚመለከት የተስሩ ስራዎችን እንዲሁም በእቅድ አፈፃፀም ወቅት የታዩ ዋና ዋና ማነቆዎች እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ዘርዘር ባለ ሁኔታ ለተስበሳቢዎች ቀርቧል፡፡
የኢትዮጲያ ብሔራዊ የፀረ-አበታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር የሆኑት አቶ መኮንን ይደርሳል በበኩላቸው ለቀጣይ ቶክዮ ኦሎፒክ ውድድር ትኩርት በመስጠት ስፖርተኞችን በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ በቂ እውቅት እንዲኖራቸው ማስቻል እና በቂ የሆነ ምርመራና ቁጥጥር ማድርግ እንደሚገባም ተናግረው በሌላም በኩል አደረጃጀታችን ወደ ክልሎች ማውረድና የስልጠና ማዕከላት ላይ ትኩረት መስጠት እንዲሁም በትምህርት ካሪኩለሙ አበረታች ቅመሞች የማካተት ጉዳይ ክትትል ማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተስጥቷቸው ሊስሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አሳብ አንስተዋል ፡፡
የኢፌድሪ ሰፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽንር አቶ ዱቤ ጅሎ ያለው ሂደት ጥሩ መሆኑን ተናግረው ዶፒንግ ጉዳይ ከድርድር የሚቅርብ ጉዳይ ባለመሆኑ ትምህርትና ስልጠናውን ወደታቸ በማወረድ ተደራሽነቱን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አያየዘውም የUNESCO Compliance ፕሮግራምንም አፈፃፀም ጥሩ እንደ ነበርና ማስተካከል የሚገቡ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚስራበት ተናግረዋል ። በሌላም በኩል በትምህርት ካሪኩለሙ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስተር ጋር በመነጋገር በጥሩ ሂደቶች ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በመጨርሻም የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር የማጠቃለያ አሳብ የስጡ ሲሆን የቀረቡት ሪፖርቶች ጥሩ እንደሆኑ ገልፀው ትኩርት የሚሹ ጉዳዮችን አስቀምጠዋል ውጫዊና ውስጣዊ የመልካም አስተዳደሮች በዕቅድ በግልጽ ማዘጋጀት ፣ የውስጥና የውጭ ኦዲት ምላሽ ማስተካከያ ማድርግ ፣ ቅንጅታዊ አስራሮችን መዘርጋትና ተግባራቶችን ተቋምን መሠረት በማደርግ መምራት ቋማቱ ትኩረት እንዲስጡበት አስፍላጊ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡