ለማሰልጠኛ ማዕከላት አካላት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ትኩረት ያደረገ ትምህርት ተሰጠ።
በኢትዮጵያ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለጂንካና ለደባርቅ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማእከላት በባህር ዳር ከዋና መስሪያ ቤቱ በሄዱ የስልጠና ባለሙያዎች ለተተኪ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛች በአበረታች ቅመሞች ወይሞ ዶፒንግ ጽንሰ ሃሳብ፣ በሚያስከትሉት ጉዳት፣ የህግ ጥሰት፣ የናሙና መሰብስቢያ ኪትና አይነታቸው (Sample of Urin testing Kits)፣ በተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማሳድጊያ ትምህርት ከመሰጠቱም በላይ የቡድን ውይይት ተደርጓል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ የማሰልጠኛ ማእከላት በአበረታች ቅመሞችወይም ዶፒንግ ዙሪያያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በእያንዳዱ ተግባራቸው የጸረ-ዶፒንግ ጉዳይን ትኩረት እዲሰጡ በማድረግ ረገድ ሚናቸውን እዲወጡ ለማስቻል ነው።
በባህር ዳር በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተተኪ አትሌቶች የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ተስትፈዋል።

By Ermias