ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምር ሊግ እግር ኳስ ክለቦች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የሚሰጠው ሥልጠና እደቀጠለ ነው ፡፡
ለሐዋሳ ከተማ እና ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሴቶች እግርኳስ ክለቦች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ቀን፡ ህዳር 13/2015 ዓ.ም
ሐዋሳ ከተማ፡ በዘንድሮ በጀት አመት በእግር ኳስ ክለቦች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጨምሮ ምርመራና ቁጥጥር ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እደሚሰራ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ገለፀ ፡፡ይህ የተገለፀው ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ሊግ ክለቦች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መከላከል ላይ በሐዋሳ ከተማ እየተሰጠ ባለው የስልጠና መድረክ ላይ ነው፡፡
ለሐዋሳ ከተማ እና ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሴቶች እግርኳስ ክለብ አትሌቶችና የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በስልጠና መድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርአት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የስፖርቱን ፍታዊ የውድድር ስራት በማዛባት ዜጎችን ለተለያየ የጤና ችግር የሚያጋልጠውን አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከል ረገድ የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችው ብለዋል፡፡
ትምህርቱን የሰጡት የባለስልጣኑ የትምህርትና ሥልጠና ባለሞያዎች ኛቸው፡፡
የስልጠና መድረክ ላይ ነው፡፡…

See more

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *