ለሐዋሳ ዩንቨርስቲ የ2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ድግሪ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች እና መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቀን ፡- መጋቢት 14/2013
ቦታ ፡- ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ
የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ- አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዳሬክተር ወ/ሮ ፋንታዩ ገዛኸኝ የስልጠና ፕሮግራሙን በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ጽ/ቤቱ የነበሩበን ፈታኝ ሁኔታዎችን በማለፍ አሁን ላይ ግንዛቤ መፍጠርና ማሳደግ ላይ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች ከስፖርቱ ጋር ያላችሁ ቁርኝት ከፍተኛ በመሆኑ በስፖርት በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ እንዲኖራችሁ ማድረጉ ጤናማ የሆኑ ተተኪ አትሌቶቸን ለማፍራት አስተዋጾ አለው ብለዋል ። አያይዘውም በዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ጽ/ቤቱ በሚያሰራጨቸው የተለያዩ መረጃዎችን በመጠቀም ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል ፡፡
ስለጠናውን 90 የሚበልጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና መምህራን ተከታትለውታል ፡፡
ስልጠናው በትምህርት እና ስልጠና ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በዶፒንግ ምንነት፣ ህግ ጥሰት፣የአትሌቶች መብትና ግዴታ፣፣ የዶፒንግ የምርመራ ሂደት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *