ለአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር እና ለአዳማ ከነማ ሴቶች ፕሪምር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ሀዋሳ ከተማ፡ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም
ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ አራሳችንን እንጠብቅ በሚል ዕርስ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለሴቶች ፕሪምር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የቀጠለ ሲሆን በዛሬው መድረክ ለአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር እና ለአዳማ ከነማ ሴቶች ክለለቦች በአበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮችና ተያየዥ አጀንዳዎች ላይ ከባለሥልጣን መስሪያቤት በሄዱ የትምህርትና ስልጠና ባለሞያዎች ሲፊና ዘርዝር ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡
የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እዳሉት ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት በ (UNESCO) በኮንቬንሽኑ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ለመተግበር በመስማማት በፊርማዋ አጽድቃ በህግ አውጭ ፓርላማዋ በአዋጅ ቁጥር 554/2009 ኮንቬንሽኑን በማጽደቅና የሀገሪቱ የህግ አካል በማድረግ ኮንቬንሽኑን ከሚተገብሩ ሀገራት መካከል ትጠቀሳለች፡፡
በዚህ ኮነቬንሽን መሰረት ብሔራዊ ፊድሬሽኖች፣ማሰልጠኛ ተቋማትና ክለቦች ከስልጠናቸው ጎን ለጎን የአበረታች ቅመሞች/ዶፒንግን የመከላከልና የመቆጣጠር ግዴታ እዳለባቸው በኮነቬንሽኑ የተቀመጡ ድንጋጌዎችንም ተግባራዊ በማድረግ ኃላፊነታቸውን መውጣት አለባችው በማለት ገልፀው ስልጠናውን በትኩረት እድትከታተሉ አደራ እላለው በማለት መደረኩን አስጀምረዋል፡፡
በስልጠና መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር እና የአዳማ ከነማ ሴቶች ክለብ አትሌቶች ፣አሰልጣኞች ፣የስነ-ምግብ፣ የህክምና ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

May be an image of 6 people, people standing, indoor and text that says 'አትሌቶች እና ለአትሌት ድጋፍ ረ-አበረታች ቅመሞች ስልጠና። Ethiopian Women's Premier hlete Support personnel. ክህዳር 08 25/2015 ን.ም November 17 December AWASA, SIDAMA 2022'

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *