ቀን፡- ሀሙስ መጋቢት 9/2013 ዓ.ም
ቦታ ፡- ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል ለገጣፎ እና አሰለፈች ሆቴል
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም በዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፡፡ 55 ያህል የብሄራዊ ቡድን አትሌቶች ስልጠናዉን ተከታትለውታል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማጎልበት፤ እራሳቸውን ከዶፒንግ እንዲጠብቁ ለማስቻል ነው፡፡
ስልጠናው በዶፒንግ ምንነት፣ ህግ ጥሰት፣የአትሌቶች መብትና ግዴታ፣፣ የዶፒንግ የምርመራ ሂደት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ነው ስልጠናው የተሰጠው፡፡
የኢትዮጲያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በ2021 በቶኪዮ ጃፓን ለሚካሔደው የኦሎፒክ ውድድር ሆቴል ገብተው ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *