ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ሊግ ክለቦች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ሥልጠና ተጀመረ፡፡
በዛሬው ዕለት ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና ለቦሌ ክ/ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ቀን፡ ህዳር 12/2015 ዓ.ም
ሐዋሳ ከተማ፡ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ሊግ እግር ኳስ ክለብ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ስራተኞች ሐዋሳ ከተማ ሥልጠና መስጠት ጀምረ፡፡
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ም/ ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እንደተናገሩት አበረታች ቅመሞችና ዘዴዎችን መጠቀም በዜጎች ላይ የጤና፣የስነልቦና የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖዎችን የሚያስከትል ነው፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከል ስፖርተኞችም ሆኑ የስፖርት ባለሞያዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችው ብለዋል፡፡ ባለስልጣኑ በአገር አቀፍ ደረጃ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤና የንቅናቄ መርኃግብሮችን ዘርግቶ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ም/ዋና ዳይሬክተሯዋ ገልፀዋል፡፡
የስልጠና መድረኩ በበአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች፤ በህግ ማዕቀፎች እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ባካሄደው የተጋላጭነት ዳሰሳ ጥናት (Doping Risk Assessment) መሰረት እግር ኳሱ ከአትሌቲከስ ቀጥሎ ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ተጋላጭ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ቀደም ብሎ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለብሄራዊ ሊግ ክለብ አትሌቶችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በስልጠናው 13ውም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ሊግ እግር ኳስ ክለቦች ይሳተፋሉ፡፡ ስልጠናው በነገው ዕለት ይቀጥላል ፡፡
መስጠት ጀምረ፡፡ …
See more