ለኢፌድሪ መከላከያ ስፖርት ክለብ አትሌቶች የሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ ትምህርታዊ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ቀን፡- አርብ ጥቅምት 20/2/2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ለመከላከያ ስፖርት ክለብ አትሌቶች በዶፒንግ ምንነት ፤በሚያስከትለው ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤ምርመራ ሂደትና በተዘረጉ ያሰራር ስርዓቶች በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የመከላከያ ስፖርት ክለቡ የአትሌቲክስ ቡድን መሪ ኮሎኔርር ሰለሞን አሸብር ሲሆኑ ት፡፡ የተዘጋጀውን ስልጠና በትኩረት እዲከታተሉ አትሌቶቹን አሳስበው መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ በአገርአቀፍና በአለማቀፍ ደረጃ የሚወዳደሩ የ5ሺ፤የ10ሺ፤የማራቶንና የርምጃ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ፤
ከ100 በላይ አትሌቶች የዛሬውን ትምህርታዊ ስልጠና ተከታትለውታል፡፡ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በተሰጠው ስልጠና ላይ ከ200 በላይ አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡