ለወርልድ ቴኳንዶ ፌድሬሽን አሰልጣኞችና ስፖርተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
አዲስ አበባ፡ ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለወርልደ ቴኳንዶ ፌደረሬሽን አሰልጣኞችኛና ስፖርተኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰርታዊ ጉዳዮቸ፤በአሰራረ ስርአቶች፤በህግ ማዕቀፎችና በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥጧል፡፡
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ም/ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እንደተናገሩት ዶፒንግ የአገራችን ስፖርት ስጋት በመሆን ላይ መሆኑን ገልጸው ባስልጣኑ በአገር አቀፍ ደረጃ የስፖርት አበረታች ቅመሞንችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የግንዛቤና የንቅናቄ መርኃግብሮችን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑንም ም/ዋና ዳይሬክተሯዋ ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው መድረክ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ህክምና ቡድን መረ ሲስተር ሃያት ከኺር እደተናገሩት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቀጣጠር በአዲስ አበባ አስተዳደር ስር ሚገኙ ለፌድሬሽኖችና ለስፖርት ባለሞያዎች፤ ለስፖርቱ ባለድሻ አካላት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡