ለጽ/ቤቱ ዓላማ መሳካት ሰራተኞች በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የደመወዛቸውን 100 ፐርሰንት ለመከላከያ ሠራዊት ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ቀን፤ነሐሴ 09/202013 ዓ.ም
አዳማ፤ሄልዝ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/Eth-Nado/ ለጽ/ቤቱ ዓላማ መሳካት ሰራተኞች በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል እንዳሉት ከሆነ በዛሬው እለት የተደርገው ውይይት ከነበሩት ክፍተቶች ትምህርት በመውሰድ ለቀጣዩ የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖረን የሚያስችል ነው ብለዋል።
የጽ/ቤቱ የእቅድና የበጀት ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ፍቅሩ ኑጉሴ ዕቅዱን ለውይይት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ከሆነ በተጠናቀቀዉ አመት ያጋጠሙንን ችግሮችን ለመፍታትና በዚህ አመት የምናከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራትን ታሳቢ አድርገን 2014 በጀት ዓመት እቅድን አዘጋጅተናል ነው ያሉት፡፡
በቀጣዩ በጀት አመት፣የምርመራ ስራው በእግር ኳስ ላይ ትኩረት ተደርጎ እደሚሰራ፣ የዓለም አቀፍ ፓርትነርሺፕ ፕሮግራም የማጠናከር፣ የትምህርትና ስልጠናውን On-Line ማድረግ፣ የህዝብ ንቅናቄና አዉትሪቺግ ፕሮግራም ማጠናከ፣የሚሰጡ ሰልጠናዎች ምን ለውጥ አመጡ የሚል impact assessment ላይ አጠናክሮ መስራት፣ተገልጋዮችን እርካታ መለካት፣የዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን(Cross-Cutting Issue)በሁሉም ስራ ክፍል ተግባራዊ ማድረግ፣ የአገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ማሳደግ፣ የዕቅድ፣ሪፖርት፣ ግምገማ ስርአት ማጠናከር ትኩረት ተሠጥቶ የሚከናወን መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አሣውቀዋል።
የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በበኩላቸው፣ከ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም በመነሳት ስኬቶችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ለይቶ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ለመስራት ታቅዶ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የተደረገ ውይይት መሆኑን አብራርተው፣ የጽ/ቤቱን የመፈፀም አቅም በማሳደግና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ዳር ማድረስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የደመወዛቸውን 100 ፐርሰንት ለመከላከያ ሠራዊት ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሀ ግብር ያከናዉናሉ።
በመጨረሻ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የበላይ አመራሮች ’’የጋራ የመግባቢ ሰነድ’’ ከየስራ ክፍሎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡