ለፋርማሲ ባለሞያዎችና አመራራች ትምህርታዊ ሴሚናር ተሰጠ
የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩ ለአንድ ቀናት የተካሄደ ሲሆን ከምሳ በፊት ’’የስፖርት አበረታች ወይም ዶፒንግ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ገፅታና ተፅዕኖ’’ በሚል ርዕስ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህር ቤት መምህርና የፋርማሲ ባለሞያዎች ማህበር ተወካይ በሰለሞን አሰፋ /ረዳት ፕሮፌሰር/ ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ተደርጓል፡፡
እዲሁም ’’በፀረ-አበረታች የህግ ማዕቀፎች ’’ ላይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ገልጻ አድርገዋል ፡፡
ከሰዓት ’’ስፖርተኞች ጉዳት በሚያጋጥማቸው ወቅት የተከለከሉ መዳኃኒቶችን በመጠቀም ተገቢውን ህክምና እዲያገኙ የሚመለከተው የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ (TUE) ’’ በተመለከተ በባለስልጣኑ የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ ቴክኒካል ኮሚቴ አባልና በጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት በዶ/ር አዲሱ መልኪ በተጨማሪ ’’ዶፒንግና የፋርማሲ ባለሞያዎች ሚና’’ በሰለሞን አሰፋ /ረዳት ፕሮፌሰር/ ትምህርት ከመሰጠቱም በላይ ሰፊ የጋራ ውይይት በማካሄድ የጋራ ግንዛቤ ለመጨበጥ ተችሏል፡፡