በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ ታዳጊ አትሌቶች እና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
(ማክሰኞ 29/03/2015 ዓ.ም) ስልጠናው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲሆን ከ40 በላይ የሚሆኑ ታዳጊ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ተሳትፈውበታል ፡፡
የኢ/ፀ/አ/ቅ/ባ/ስ/ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛኸኝ የስልጠናውን ፕሮግራም በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ተቋማችን በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር መከላከልና መቆጣጠርን አላማ በማድረግ የተቋቋመ ሲሆን የዶፒንግን አስከፊነት በተለይ ለታዳጊ አትሌቶች ማሳወቅ ስፖርተኞች ላይ ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዚህም ስልጠና ዋነኛ አላማ ይህን ታሳቢ በማረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንንም ጠቁመዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም ተተኪ አትሌቶች ስለ ዶፒንግ ያሉትን መረጃዎች ትኩረት ሰጥተው በማንበብና በመጠየቅ በዶፒንግ ምክንያት ሊደርስባቸው ከሚችሉ የጤናና ተያያዥ ችግሮ እራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
ስልጠናው በዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትሉት ጉዳቶች ፤የህግ ጥሰት ፤ በምርመራ ሂደቶች እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን የባለሥልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ባለሞያ የሆኑት በአቶ ሐብታሙ ካሱ አማኝነት ለስፖርተኞች ገለፃ ተደርጓል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *