በሴቶች ስኬታማ ተሳትፎ የተቋማችን ውጤታማነት እናረጋግጣለን!!!
በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጲያ ጸረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የሴቶች ፎረም 1ኛ ዓመት የውይይ መድረክ ተጠናቀቀ ፡፡
የኢትዮጲያ ጸረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፎረሙን በደገፍ የሴቶችን ተሳትፎ ትኩረት ሰጥቶ መሄድ ተገቢ በመሆኑ የፎረሙ አመራሮች አመስግናለው በቀጣይ የተጀመሩ ጉዳዮችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡ አያይዘውም በዚህ ጉዳይ ተቋማቶች በስፋት የሚሰሩ መሆን አለባቸው በግለሰቦች የታጠሩ ሳይሆን ሴቶችን በማሳተፍ ወደ ትልቅ መድረክ ይዘው የሚሄዱ ሊሆኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል ፡፡
በተቋማችንም የሴቶች ቁጥር ከወንዶች ከፍ የሚል በመሆኑም ትልቅ ኩራት ይሰማናል በመሆኑም ተወዳዳሪ በመሆን እራሳችሁን በማሳደግ በአቅማችሁ አሳምናችሁ የምትፈልጉትን ነገር መያዝ እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ቁርጠኝነታችሁን በማሳየትና በማሳመን እናንተን ይዘን የተቋማችን ውጤታማነት እናረጋግጣለን በዚህም በቀጣይ 5 ዓመት መንግስተ ሊሰራቸው ያቀዳቸው ጉዳዮች ብዙ ከመሆናቸው አንጻር ለተልዕኳችን መሳካት እጅ ለእጅ ተያይዘን መሄድ ይገባናል በማለት ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በነበሩት አጠቃላይ የውይይት መድረኩ ላይ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘት መቻላቸውን እና በቀጣይ በሚኖራቸው የቤተሰብም ሆነ የስራ ህይወታቸው ላይ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው የፎረሙ አባላት ገልጸዋል፡፡ የፎረሙን አቅም በማጠናከር ጥሩ ጅማሬዎቻችንን በማስፋት በ2014 በጀት አመት የተሻሉ ስራዎችን መስራት እንደሚገባም በአስተያየታቸው ጠቁመዋል ፡፡
በመጨረሻም በተለያዩ የመዝጊያ ፕሮግራሞችን በማካሄድ የፎረሙ 1ኛ ዓመት ክብረ በዓል ተጠናቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *