በስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች(Supplements) ዙሪያ ለስፖርት ህክምና ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ቦታ፤ የአማራ ስፖርት ኮሚሽን ስብሰባ አዳራሽ፣ባህርዳር ከተማ
እሁድ ግንቦት 22/ 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ETH-NADO/ በአማራ ክልል የስፖርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች በስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplements) ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከአማራ ክልል ሰፖርት ኮሚሽን ጋር በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡
ትምህርቱን የሰጡት ወ/ሮ ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፍተኛየህክምና ባለሞያ ሲሆኑ፤በገለጻቸው፤የስፖርት ድጋፍ ሰጪስነ ምግቦችን (Supplements) አለመጠቀም፤ በአምራች ድርጅቶች ውስጥ የመበከል እድላቸው ሰፊ ሰለመሆኑ፣ የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮችን ም የሚጨምሩ መሆናቸው፤ምንም አይነት ህግ ያልወጣላቸውና በቂ ቁጥጥር የማይደረግላቸው እና ከላያቸው ላይ የሚፃፈው መግለጫ በውስጣቸው የያዙትንነ ንጥረ-ነገር በትክክል የማያሳይ በመሆናቸው፤ለአበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ሊያጋልጡ ይችላሉ ብለዋል፡፡
በመቀጠል አትሌቶች ማንኛውም ድጋፍ ሰጭ ምግቦችን ከመጠቀማቸው በፊት ባለሞያ ማማከር፣ጥንቃቄ ማድረግ እደሚገባ አሰረድተዋል፡፡
የትምህርቱ ትኩረት የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ምንነት፤ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ስላላቸው ግኑኝነት፤ ከአሰልጣኝና ከአትሌቱ ምን ይጠበቃል፤ ስልጠና በኮረና ወቅት በሚሉ ኮሮና እና ጭንቀት፤ከሮናና የሰውነት ክብደት በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ነው፡፡
አትሌቶች ብቃታቸዉን ለማሻሻል ድጋፍ ሰጭ መድኃኒቶችን/ቪታሚን (Supplements) ይልቅ ተመራጩ በቀላሉ ከአካባቢያቸው በሚያገኞአቸው ተፈጥሮአዊ ምግቦች ላይ ቢያተኩሩ እደሚገባ በዚህ ረገድ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎች አትሌቶችቻቸው የማስተማር፤ የመደገፍ ሙያዊ ኃላፊነትታቸውን እዲወጡ ባለሞያዋ ጨምረው ገልፁዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ከ30 በላይ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎች፣ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡