በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ባለሙያዎች እና የክፍለ ከተማ የስፖርት ባለሙያዎች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

ቀን፡- ሐሙስ /4/06/2013 ዓ.ም
ቦታ፡-አዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል (ወወክማ)/ አደራሽ

በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ባለሙያዎች እና በአስሩም ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የስፖርት ባለሙያዎችና አመራሮች በአበረታች ቅመሞችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት አማካኝነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ ፡፡

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ህክምና ቡድን መሪ ወ/ሮ ሀያት ኪያር የስልጠናውን ፕሮግራም በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በስፖርት በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ ለባሙያዎች የግንዛቤ ስልጠናውን መስጠት ጤናማ የሆኑ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የዚህ ስልጠና ዋነኛ አላማ የስፖርት ባለሙያዎች በዶፒን ዙሪያ የተወሰኑ ግንዛቤዎችን በመያዝ በተዋረድ ወደ እታች በማውረድ እውቀቱን በማስተላለፍ መስራት እንዲችሉ ለማድርግ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የፀረ-ዶፒን እቅድ በማውጣት በመስራት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ተከታታይ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በስፋት እንስራልን ለዚህም የእናንተ ተሳትፎ በአላፊነት ሊሆን ይገባል በማለት ለተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ሲሆን ስልጠናው የተስጠው በኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች አማካኝነት ነው ፡፡

ስልጠናው በሁለት ዙር ሲስጥ ወደ 150 የሚጠጉ የስፖርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ተገኝተው ተከታትለውታል ፡፡
በዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትሉት ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤ እና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም ከስልጣኞች ጥያቄ እና አስተያየቶች ተነስተተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ዶፒንግን በጋራ እንከላከል!!!

May be an image of one or more people, people standing and indoor May be an image of 1 person and standingMay be an image of one or more people and people sittingMay be an image of 2 peopleMay be an image of 3 people and people sitting

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *