በጽ /ቤቱ የአስር አመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
ቀን፡29/1/2013ዓ.ም
ቦታ፡- አዳማ ጀርመን ሆቴል
በዛሬው የሁለተኛ ቀን የውይይት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ማናጅመት አባላትና ሰራተኞች የአስር አመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛኽኝ ውይይቱን በመሩበት ወቅት እዳመለከቱት የውይይቱ ዓላማ የጽ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች የአስር አመቱን መሪ ዕቅድ ላይ ግባት ለማሰባሰብና የጋራ ግንዛቤ እዲጨብጡ ለማስቻል እደሆነ አመልክተዋል፡፡
የእቅድና በጀት ደይሬክቶሬ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዲሳ የጽ/ቤቱን የቀጣይ በአስር አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ(20123-2020) ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ጽ/ቤቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመከላከልና ለቆጣጣር እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ለማጎልበት በአበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የላቀ ሚና መጫወት እደሚጠበቅበት ም/ ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት አሳስበዋል፡፡
በቀጣይ በኣስር አመቱ መሪ እቅድ ዙሪያ ከባለድረሻ አካላትና ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት እንደ ሚካሄድና ግዕባት እደሚሰባስብ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በባላስድ ስኮርካርድ ዙሪያ በጽ/ቤቱ የሰው ኃብት ፤ግዥና ንብረት አሰተዳደር ዳ/ዳይሬክተር በአቶ ፍቅሩ ንጉሴ ገለጻ ተድረጓል ፡፡
በነገው ዕለት የ3ኛ ቀን ፕሮግራም በ2013 በጀት አመት አቅድ ላይ ውይይት ይካሄየዳል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *