በፀረ-አበረታች ቅመሞች እቅስቃሴ ላይ አስተዋፆ ላበረከቱ የዕውቅና ሠርተፊኬት የመስጠት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
4ኛው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጉባኤ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል አገራችን የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴና የአምስት አመት ጉዞና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ገለፃና ማብራሪያ ባደረጉበት ወቅት እዳሉት የጉባኤው ዓላማ የማስተባበርና መደገፍ ሥራ ለመስራት ነው፡፡
በአሁን ወቅት አለም አቀፍ ደረጃ ስፖርቱን ከማስፋፋትና ልማቱን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን አበረታች ቅመሞችን መቆጣተር ስራ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጉዳይ የጤና፣የህግ፣ ጤናማ አትሌቶችን የማፋራትና ሌሎች ጉዳዮች ያሉበት መሆኑን ጨምረው አብራርተዋል፡፡
በተመሳሳይ የኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻፒዎና ውጤት እዲሁም የአረንጓዴው ጎርፍ ታሪክ የዚህ ጉባኤ ዋና ጉዳይ እደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ዋና ዳይሬክተሩ የባለስልጣኑን የቀጣይ 2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ገለፃ አድረገዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የፀር -አበረታች ቅመሞች በለሥልጣን በፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ አስታዋፆ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና መስጠትፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በዚህው መሰረት ለዶ/ር አያሌው ጥላሁን፣ ለአቶ ይርሳው ዘውዴ፣ ለወ/ሮ መሰረት ተሾመ እና ለአቶ ቢኒያም ጌታቸው የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
በጉባኤው ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተለያዩ ክልሎችና የአገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን ሌሎችም ተሞክሮውን በመውሰድ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማካሄድ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ተመላክቷል።
የአለም አቀፍ ተቋማት የፀረ- ዶፒንግ አመራሮችም በጉባኤው ላይ መልዕክቶቻቸውን አስተላልፈዋል።
ሽልማቱን የሰጡት ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ የባህልና ስፖርት ሚኒሰተር የስነ ጥበብና የኪነ ጥበብ ሚኒስተር ዴኤታ ናቸው፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *