በፀረ-አበረታች ቅመሞች የሕግ ማዕቅፎች የመጀመሪያ ረቂቂ ሰነድ ላይ የባለድርሻ አካላት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ አዝማን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
ህዳር 23 / 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የፀረ-አበረታች ቅመሞች የሕግ ማዕቅፎች ቀረፃ የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ ላይ የሴክተሩ ዋነኛ የባለድርሻ አካላት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲሰ አበባ ከተማ አዝማን ሆቴል እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በመድረኩ የኢፊድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስተር የስፖርት ልማት ዘርፍ ዴኤታ አባሳደር መስፍን ቸርነት መልዕክት በማስተላለፍ በይፋ ከፍተውታል ።
የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ የተላያዩ አግባብነት ያላቸውን የመረጃ ምንጮችን መሰረት በማድግ ለውይይት መነሻ የሚሆን ’’የፀረ-ዶፒንግ የህግ ማዕቅፍ የመጀመሪያ ረቂቅ ሰነድ በማዘጋጀት ለሴክተሩ ልማት ዋነኛ ተዋንያን ለሆኑት ባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር የማዳበሪያ ግባኣቶች እዲያመነጩ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮንን ይደርሳል ገልፀዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የኢፊድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስተር የስፖርት ልማት ዘርፍ ዴኤታ አባሳደር መስፍን ቸርነት ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮነን ይደርሳል፤የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝና፣የባህልና ስፖርት ሚኒስተር የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮት ዳይሬክተሮች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በድምሩ 60 የሚሆኑ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ውይይቱ ለአንድ ቀን እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡
መድረኩ ከምሳ በፊት የፀረ-አበረታች ቅመሞች ረቂቅ የፖሊሲ ሰነድ በአቶ ፍቅሩ ንጉሴ እና የማቋቋሚያ ደንብ በወ/ሮ ሜሮን ጌታቸወ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ከሰዓት በቀረቡት ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል።