በ39ኛው ጃን-ሜዳ ሃገርአቋራጭ ውድድር ላይ የፀረ-ዶፒንግ የቅስቀሳና Outreaching ፕሮግራሙ ተካሄደ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን (ETH-ADA) ለ39ኛ ግዜ የካቲት 06/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በተከሄደው የጃን – ሜዳ እና የምስራቅ አፈሪካ ኢንተርናሽናል ሃገር አቋራጭ ውድድር ላይ ለተሳተፉ የስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች እንዲሁም የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም አካሂደዋል፡:
በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ የቅስቀሳና ፕሮሞሽን ማቴሪያሎች ፤ ብሮሸሮች ፣ የፊት ማስክዎች፤ ለስፖርተኞች ፣ ለስፖርት ባለሞያዎች፣ለስፖርት አመራሮችና ሌሎችንም ተሳታፊዎች የተሰራጨ ሲሆን በተለይ አሳታፊ የሆኑ፤አትሌቶችን በቀላሉ ግንዛቤ እዲጨብጡየሚያስችል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል በተጨማሪ የተለያዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ባነሮች ተዘጋጅተው ለዕይታ በሚያመች ቦታዎች እዲሰቀሉተደርጓል::
በውድድሩ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት፤ከክልል፤ ከተማ አስተዳደሮች፤ ከክለቦች፤ ከዩኒቨረሲቲዎች፤ ከአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፤ ከተቋማትና የግል ተወዳዳሪዎች የተውጣቱ በርካታ አዋቂ እና ወጣት አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡
Ethiopia Anti-Doping Authority (ETH-ADA) carried out an Anti-Doping Outreach program on the 39th Jan-Meda and 1st East Africa International Cross-Country Competition held in Addis Ababa on February 13/2020, to raise awareness amongst athletes, athlete support personnel, and sport leaders as well as to create mass mobilization against doping.
Athletes and Athlete support personnel drawn from East African countries, City administration, Clubs, Universities and Athletics training centers, Institution plus private competitors participated in this Championship.
Since 2017, ETH-ADA Anti-Doping Outreach Program has been on-hand during the International and National Games, and other Major Events, to raise awareness amongst athletes and their followers about doping-free sport; and, to engage them more as part of the solution.