የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት እና ደም ለመለገስ ቃል ገቡ፡፡
የፅ/ቤታችን ሰራተኞችና አመራሮች በተቋሙ የ2013 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም እና በ2014 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከነሐሴ 08/2013 ዓ/ም ጀምሮ በአዳማ ከተማ የተወያዩ ሲሆን ባሳለፍነው በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችንና ጠንካራ ጎኖችን በአግባቡ መለየት ተችሏል፡፡
በተለይም ከ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጋር በተያያዘ ሰፊ የሆነ የቅድመ ዝግጅት እና የምርመራና ቁጥጥር ተግባራትን ማከናወን የተቻለ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡
ሌሎችም የትምህርትና ስልጠና፣ የምርመራና ቁጥጥር እንዲሁም የተቋማዊ አቅም ግንባታ እንቅስቃሴዎች ተገምግመዋል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያም ሰፊ ውይይት ማድረግ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችም ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተካሄደ ባለው አገር የማዳንና ህግ የማስከበር ዘመቻ ዙሪያ በመወያየት ለመከላከያ ሰራዊታችን የአንድ ወር ደመወዛቸውን በመስጠትና ደም በመለገስ ደጀንነታቸውን ለማረጋገጥ እና የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡