አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግን) በመከላከል ረገድ የህክምና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡
ቀን፡- መጋቢት 13/ 2013 ዓ.ም
ሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል
በሐዋሳ ከተማ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ለህክምና ፤ የስነ-ምግብ እና ወጌሻ ባለሞያዎች በዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብሩክ ቡናሮ ባደረጉት ንግግር የዶፒግ ጉዳይ እንደ አገር አንገብጋቢ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም ዶፒንግን ከመከላከል አንጻር የህክምና ባልሙያዎች ትልቅ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የዛሬው መድረክ ወሳኝ በመሆኑ በንቃት በመከታተል ያገኘነውን እውቀት በማጋራት ተግባራዊ ማደረግ እንደሚገባ በንግግራቸው ጠቁመዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ምክትል ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በበኩላቸው የጽህፈት ቤቱ አላማ ግንዛቤን በመፍጠር ዶፒንግን በመከላከል ንጹህ ስፖርትን ማስፈን ሲሆን ጽ/ቤቱ የስፖርት ጸረ- አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ ) በስፖርቱ ውስጥ በሚያስከትላቸው ጉዳቶች ዙሪያ ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነዉም በአገር አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያደረገ ያለውን ጥረት ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡ ስለሆነም ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ያገኘነውን እውቀት በተገቢው መንገድ ማስተላልፍ እንደሚገባ ለተሳታፊዎች አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን ከሲዳማ ክልል እና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል የተወጣጡ 55 የሚጠጉ የህክምና የስነ-ምግብ እና የወጌሻ ባለሞያዎች ተገኝተዋል፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤ በስፖርትድጋፍ ሰጪ ፤በአሰራር ስርአቶች፤ በአትሌቶች መብትና ግዴታዎች እና ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፣የህግ ጥሰት ዙሪያ በጽ/ቤቱ ትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች ገለጻ ተደርገዋል፡፡
በከሰኃት በኋላ መርሃ-ግብር በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ የቡድን ውይይት ከተደረገ በኃላ በቡድኑ ተወካዮች በኩል ለቤቱ ይቀርባል፡