የፋርማሲው ባለሙያዎች አትሌቶች ተገቢ ጥንቃቄ እዲያደርጉ የሚያስችሉትን ሙያዊ እጋዛዎች እዲያገኙ ማድረግ እደሚገባቸው ተገለፀ
በአዲሰ አበባ የተደረጉ ጥናቶች 50% የሚሆነው ፋርማሲሲት ሰለ ‹‹ዶፒንግ›› ግንዛቤ የለውም – የኢትዮጵያ ፋርማሲዎች ማህበር ፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፋርማሲ ባለሞያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ ፋርማሲ ባለሙያዎች ‹‹በዓለምና አገር አቀፍ የዶፒንግ ተጋላጭነት፤በስፖርት የተከለከሉ መዳኃኒቶች ዝርዝር፡ የፋርማሲ ባለሞያዎች ሚና እና የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ (TUE)›› በሚል ርዕስ ሴሚናር የተከሄደ ሲሆን እዲሁም በፀረ-ዶፒንግ ህግ ማዕቅፎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-ዶፒንግ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ የተመለከቱ ፅሁፎች በባለሞያዎች ትምህርት ከመሰጠጡም በላይ ከተሳታፊዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ፡፡
የመድረኩ ዋና ዓላማ ከኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ጋር በቅንጅት ሲዘጋጅ የባለሞያዎችን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ እና በየደረጃው ባሉ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ግንዛቤ ለማጎልበትና የፋርማሲው ሴክተር ህጋዊ መስመሩን ብቻ ተከትሎ በመስራት በፀረ-ዶፒንግ ትግሉ ረገድ የድርሻቸውን እዲወጡ ለማስቻል ሲሆን እዲሁም ባለስልጣኑ ሊያዘጋጀው በዕቅድ የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-ዶፒንግ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ግብዓት ለመስጠት ነው፡፡
‹‹Overview on Global and National prevalence of doping እና Anti-doping and sport Drugs: Role of pharmacists’›› በሚል እርዕስ ትምህርቱን የሰጡት የኢትዮጵያ ፋርማሲ ባለሞያዎች ማኅበር የጥናት ምርምር ኃላፊና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋርማሲ ት/ቤት የፋርማኮሎጂ መምህር በሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሰለሞን አሰፋ ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ፡፡
በተለይ ’’ ድጋፍ ሰጭ ምግቦችን ( Nutrient supplements) አስመልክተው ረዳት ፕሮፌሰሩ እንዳብራሩት ድጋፍ ሰጪ ምግቦችን (supplements) ትክክለኛነታቸውን ለማረጋጋጥ መተኮር ያለባት የካንፓኒውን ዌብ-ሳይት ሳይሆን ሳይንትፊክ (scientific) ዌብ-ሳይቱ ላይ ነው ትክክለኛነታቸውን ረጋገጥ የሚቻለው፤ሌላው መታየት ያለበት ካንፓኒው ከዚህ በፊት ያልተቀጣ መሆኑን ማረጋጥ እደሚገባም ገልፀዋል ፡፡
አያይዘው ፋርማሲ ባለሞያው የአትሌቱን ንቃተ ህሊና መሰረት አድረጎ ነው መዳኃኒት መታዘዝ ያለበት ብለዋል፡፡
ዶፒንግን በተመለከተ፡ የፋርማሲስቱ ሚና ናሙና መውሰድ፣ ደጋፊ መሆን ፣ተነሳሽነት (self-motivated ) መሆን አለበት፤ብለዋል ፡፡
ፋርማሲ ባለሞያዎች ማኅበር ሚና በተመለከተ በካሪኩለም ላይ እዲገባ ማድረግ፣ፖሊሲ እዲወጣ የመደገፍ ስራ ከባለስልጣኑ ጋር በቅንጅት እደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
ማኅበሩ በአዲሰ አበባ በአደረኩት ጥናቶች 50% የሚሆነው ፋርማሲስት ሰለዶፒንግ ግንዛቤ እደሌላቸው እረጋግጫለው ብሏል ፡፡
በተጨማሪ ማንኛውም አትሌቶች ጉዳት በሚያጋጥማቸው ወቅት የተከለከሉ መዳኃኒቶችን በመጠቀም ተገቢውን ህክምና እዲያገኙ በተዘረጋው የአሰራር ሥርዓት ላይ በባለስልጣኑ የህክምና ፍቃድ አሰጣት፡ Therapeutic Use Exemption (TUE) ኮሚቴ ሰብሳቢና በጥቁር አንበሳ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻልሊሰትና የኩላሊት ሐኪም አዲሱ መልኬ (ዶ/ር) ሰፊ ገላፃ ተደርጓል፡፡
በአዳማ በተካሄደው ሴሚናርላይ፡በጥናት በተለዩ አትሌቶችና ማሰልጠኛ ተቋማት በሚበዙበት በአራዳ፣በቂርቆስ፣በየካና በአቃቂ ቃሊቲ ከክፍለ ከተሞች አካባቢ የሚገኙ የፋርማሲ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *