ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት አጠቃላይ ሰራተኛው በተገኘበት የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም እና በቀጣይ የ6 ወር ዕቅድ ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል ፡፡
ቀን፡- ማክሰኞ ጥር 09/2015 ዓ.ም
አዳማ ከተማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን/ ETH-ADA / በ2015 የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ የተቋሙ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች ባሉበት ውይይትና ግምገማ አካሂዷል ፡፡
የውይይት መድረኩ ከጥር 09-10 / 2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በዚህ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል እና የተቋሙ ምክትል ዋና ዳሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ተግኝተዋል ፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ስድስት ወራት ያቀድናቸውን ስራዎች በምን አግባብ እንደፈጸምን በጥልቀት በማየት የነበሩን ክፍተቶች እና ጥንካሬዎችን በመፈተሽ የነበሩብንን ክፍተቶቻች በመሙላት ጥንካሬዎቻችንን አጠንክረን ይዘን ለቀጣይ ዕቅዳችን ጥሩ አቅም የምንፈጥርበት የውይይት መድረክ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይህ መድረክ በዛሬ ዕለት የተቋሙ መጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት በ ወ/ሮ ስርጉት በየነ የተቋሙ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቀጣይ 6 ወር ዕቅድ በአቶ ጀንበር ነጋሽ የዕ/ዝ/ክ/ግ/ቡድን መሪ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል ፡፡
May be an image of 3 people, people standing, people sitting and text that says 'WIFI-Pass Kmhall@Big'
May be an image of 9 people, people standing and indoor

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *