ከደብረ ብርሃን ከተማ አሰተዳደር የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ’’የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን’’ ጉዳይ በስልጠና ካሪኩለም ውስጥ አካቶ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ከስፖርት አመራሮችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ ፡፡
በየደረጃው የስልጠና ማዕከላት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ በአትሌቶች ሰብዕ እና ባህሪ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ትኩረት ስጥተው ሊሰሩ እደሚገባ ተገለፀ፡፡
የደብረ በርሃን ከተማ አስተዳደር አተሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የፀረ-አበረታች ቅመሞችን ጉዳይ በስልጠና ካሪኩለም ውስጥ አካቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ በምሳሌነት የሚታይ ተግባር እያከናወነ መሆኑንም ምልከታ ተደርጓል፡፡
ጥቅምት 05/2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-NADA/ የአተሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል የፀረ-አበረታች ቅመሞችን ጉዳይ በስልጠና ካሪኩለም ውስጥ አካቶ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የስፖርት ባለሞያዎችና የአትሌቶች ተወካዮች ድርሻም ምን መሆን እንዳለበትም ውይይት ተደርጓል፡፡
ለስልጣን መስሪያቤቱ ለአትሌቲክሰ ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚሠጠው የግናዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደተጠበቀ ሆኖ በዋናነት ግን የሁለትዮሽ ትብብር ጋር ያተኮረ ግንኙነት አስፈላጊ እንደሆነ በውይይት መድረኩ ተጠቆመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-NADA /ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን የሚመለከቱ ጉዳዮች በስፖርት የስልጠና ማዕከላት መደበኛ የስፖርት ስልጠና ካሪኩለሞች ውስጥ እንዲካተት የማድረግ፤የማጣቀሻ ሰነድ የማዘጋጀት፣ ለአሰልጣኝ ባለሞያዎች በሁለት ዙር ስልጠና መሰጠቱን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ፣ በውይይት መድረኩ ላይ በተሳታፊዎች የተዘረዘሩት አስተያየቶች፣ ቀጣይ ሥራ አቅም የሚሆኑ በመሆናቸው በግባዕትነት ተወስደዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *