የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና ከሲዳማ ክልል ለተወጣጡ ለህክምና ፤ የስነ-ምግብ እና ወጌሻ ባለሞያዎች በተዘጋጀ መድርክ ላይ ‹‹የስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplements) ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጋር ያላቸው ግኑኝነትና በተያያዥ ርዕሶች›› ላይ በበይነ መረብ (zoom meeting) አማካኝነት ስልጠና ተሰጠ፡፡
መጋቢት፡- 14/2013 ዓ.ም /
ሐዋሳ፡- ሴንትራል ሆቴል
ስልጠናውን የሰጡት ወ/ሮ ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የህክምና ባለሞያ ናቸው፡፡
የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ምንነት፤ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ስላላቸው ግኑኝነት፤ በተከለከሉ መድሀኒቶች ዝርዝር ፤ በህመም ምክንያት የሚፈቀዱ የተከለከሉ ቅመሞች ፤ የህክምና ስርዓቶችና መፍቀጃ ቅጽ ዙሪያ እንዲሁም እንዴት እንጠንቀቅ ? እንዴትስ እናስጠንቅቅ? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ትኩረት የተደረገባቸው ናቸው ፡፡
በተጨማሪም ባለሙያዎቹ በቡድን የተወያዩበትን ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ከባለሙያዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች በምክትል ዳሬክተሯ በወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡