ወጣት ተተኪ አትሌቶች ከስፖርት አበረታች ቅመሞች እራሳቸውን በመጠበቅ በህይወታቸው ላይ ከሚደርሰው አደጋ ሊጠነቀቁ ይገባል ተባለ፡፡
ግንቦት 27/2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ለኢትዮጲያ ወጣቶች አካዳሚ አትሌቶችና አመራሮች በዛሬው እለት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ ፡፡
የኢትዮጲያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳሬክተር አቶ አንበስ እንየው በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደተናገሩት ተተኪ አትሌቶች ስለዶፒንግ በቂ ግንዛቤ መያዝ በስፖርቱ ዘርፍ ነገ ሊደርሱበት ከሚያስቡት ትልቅ ደረጃ ለመደረስ ግንዛቤውን መያዝና እራሳቸውን መጠበቅ ይገባችዋል ብለዋል፡፡
በተለይ በእኛ የስፖርት የስልጠና ማዕከል ላሉ ወጣት ስፖርተኞች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ለመስራ በመታሰቡ ጽ/ቤቱን አመሰግኜ በዚህም ወጣት ስፖርተኞች ይህንን አጋጣሚ በደንብ በመጠቀም በአበረታች ቅመሞች ላይ የሚሰጠውን ስልጠና በጥሞና መከታትል እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛኸኝ በበኩላቸው ጽ/ቤታችን በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር መከላከልና መቆጣጠር አላማ በማድረግ የተቋቋመ ሲሆን የዶፒንግን አስከፊነት ለእናንተ በማሳወቅ ስፖርቱን እና ስፖርትኞችን ሊያጠፋ ከሚችለው ዶፒንግ ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም ወጣት አትሌቶች እራሳቸውን ከዶፒንግ በመጠበቅ ከሚደርስባችሁ የጤናና ተያያዥ ችግሮ መዳን እንደሚገባ ተናግርረዋል ፡፡
ስልጠናው ከዛሬ ግንቦት 27- 28/2013 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከ100 በላይ የሚሆኑ ወጣት አትሌቶች እናየማዕከሉ የአስተዳደር ሰራተኞችና አስልጣኞች ተገኝተውበታል ተከታትለውታል ፡፡
በጠዋቱ የስልጠና መርሃ-ግብር በጽ/ቤቱ የትምህረት፣ ስልጠና ምርምር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ፈለቀ ዋለልኝ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በገለፃቸውም በዶፒንግ ምንነት፣ የተዘረጉ የስራር ስርአቶች፤የህግ ጥሰቶች፤ በሚያስከትሉት ጉዳቶች፤ በአትሌቶች መብትና ግዴታ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በሚሉ ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ ዘርዘር ያለ ገለፃ አቅርበዋል፡፡
ከምሳ ዕረፍት በኃላ በስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplments) ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና በወ/ሮ ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፍተኛ የህክምና ባለሞያ ተሰጥቷል ፡፡
የትምህርቱ ትኩረት የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ምንነት፤ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ስላላቸው ግንኙነት፤ ከአሰልጣኝና ከአትሌቱ ምን ይጠበቃል፤ በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ሰጥተዋል ፡፡
በመጨረሻም ከአትሌቶቹ ጥያቄዎች አንስተው የጋራ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ስልጠናው በነገውም እለት የሚቀጥል ይሆናል፡፡