በቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፉ ለሚገኙት የሀዋሳ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች የህክምና ባለሙያዎች ፣ አሰልጣኞች እና አመራሮች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ሰልጠና ተሰጠ ፡፡
ቀን ፡-ግንቦት 10/2013 ዓ.ም
ሴንትራል ሆቴል ሀዋሳ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ለተጫዋቾቹ መልዕክት በማስተላለፍ መድረኩን በይፋ ከፍተውታል፡፡
በንግግራቸውም የኢትዮጲያ ብሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዶፒንግን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተቋቋመ እንደሆነ ተናግረው የዚህም ስልጠና አላማ እግር ኳሱን ከዶፒንግ በመከላከል የተጫዋቾችን ግንዛቤ ማሳደግ እና ንጹህ ስፖር መንፈስ እንዲኖር ለማስቻል መሆኑን ዳሬክተሯ በመክፈቻ ንግግራቸው ጠቁምዋል ፡፡
አበረታች ቅመሞችን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስፖርተኞች እየተጠቀሙ ይገኛሉ በዚህም ተቋማችን ከሁሉ በፊት ማስተማርን ትኩረት አድርጎ እየሰራ በመሆኑ ዛሬ የሚሰጣችሁን የግንዛቤ ማስጨበጫ በንቃት በመከታተል እራሳቸውን ከዶፒንግ በመጠበቅ ከሚደርሱባቸው ተያያዥ ችግሮች ለመዳን ግንዛቤውን መያዝ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው በትምህርትና ስልጠና ዳሬክቶሬት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መስረታዊ ጉዳዮች፤ በየደረጃው ባሉ የአሰራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቶች ፤ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ በተከለከሉ የስፖርት አበረታች ቅመሞችና ዘዴዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
40 የሚሆኑ የእግር ኳስ ቡድኑ ተጫዋቾች እና ባለሞያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
የሀዋሳ የእግርኳስ ክለብ በ2013 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ከሚሳተፉ ክለቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን በ31 ነጥብ በ6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ፡፡