የስፖርት ማህበራት አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በቂ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተጠቆመ።
ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም
አዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የስፖርት ማህበራት አመራሮችና ከተለያዩ የስፖርት ማሰልጠኛዎች የተወጣጡ አካላትን ያሳተፈ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮንን ይደርሳል በዛሬው እለት ለተሳታፊዎች ጽ/ቤቱ ከየት ወዴት? የሚል ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል ።
ዋና ዳይሬክተሩ በገለጻቸው የጽ/ቤቱ አጀማመርና አሁን የደረሰበትሁኔታ፤ አደረጃጀትና አሰራር፤ ተቋማዊነጻነት
፤ የኢትዮጲያ ተሞክሮ ለሌሎች አገራት ማጋራትን በሚመለከት ፤ የባለ ድርሻ አካላት ሚና ምን መሆን አለበት የሚሉ ጉዳዩችን በተጨማሪም የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ በአገራችን ስፖርት መሰረታዊ ችግር እንደሆነ ፤ የኢፌዲሪ መንግስት ይህን በአግባቡ በመገንዘብ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለዚህም በአገራችን እስካሁን ያለው አፈፃፀምም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ በመሆኑን በቀጣይም ይህ እንቅስቃሴ በተጠናከረ መንገድ መቀጠል እንደሚገባ በገለጻቸው ላይ አብራርተዋል ::
የስፖርት ማህበራት ባለሞያዎች ከምንም በላይ የዶፒንግ ጉዳይ በዋናነት የሚመለከታቸው በመሆኑ በመጀመሪያ ራሳቸው ከችግሩ ነፃ በማድረግ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መጫወት የሚገባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡
አያይዘዉም አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን በመዘርጋት የፀረ ዶፒንግ ጉዳይን የእቅዳቸው አካል በማድረግና አስፈላጊውን ሐብት በመመደብ ትኩረት ሰጥተው ዶፒንግን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ከዚያ ባለፈ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በዚህ ዓመት የፀረ አበረታች ቅመሞችን በተመለከተ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት መደረጉን የብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ተናግረዋል፡፡ ይህም ታዳጊዎች ስለጉዳዩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ግንዛቤው እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡
ከምሳ እረፍት በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በፀረ-ዶፒንግ የህግ ማዕቅፍ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፊና ዘርዘር ያለ ገላፃ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተጥቶባቸዋል የእለቱ ውይይ ተጠናቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *