የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካትተው ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተግባራዊ እደሚደረግ ተጠቆመ ፡፡
የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ትምህርት ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሁም በስፖርት የማሰልጠኛ ማዕከላት መደበኛ የስፖርት ስልጠና ካሪኩለም ውስጥ እዲካተት ተደረጎ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርጿል፤ በቀጣዩ ዓመት ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።
የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር አቶ መኮነንን ይደርሳል የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ተካትተው ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ መካተቱ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከማምጣቱም በላይ ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞችና ንፁህ ስፖርት ለማስፋፋት የሚረዳ መሆኑንም ዋና ዳይሬከተሩ ገልጸዋል።
ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ነፃ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞች ተፈጥረውና ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ተወዳድሮ ማሸነፍ ባህል ለማድረግና ዶፒንግን በየደረጃው ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሎች/የከተማ አስተዳደሮች እና በፌዴራል ደረጃ በሚካሄደው የመማሪያ መፅሐፍ (Text Book) ዝግጅት ላይ ባለስልጣኑ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ላይ እደሚገኝ ፡፡ ለክልሎችና የከተማ አስተዳደሮችም አስፈላጊ መረጃዎች ተዘጋጅተው ግብዓት እንዲሆኑ መላኩን ዋና ዳይሬከተሩ ጨምረው ገልጸዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በክለቦች፤በብሔራዊ ቡድንና በስፖርት የማሰልጠኛ ማዕከላት መደበኛ የስፖርት ስልጠና ማኑዋል ውስጥ ተካትተው ከስፖርቱ ጎን ለጎን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለተተኪ ስፖርተኞች ስልጠናው እንዲሰጥ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ እደሚገኙ ተገልፃል፡፡
May be an image of 1 person and sitting

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *