ከተለያዩ ተቋማ ለተወጣጡ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሞያዎች (DCOs and BCOs) ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ::
ህዳር 25/2013
አዳማ ራስ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-Nado) የስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራ በተሻለ ለማካሄድና ቀጣይነት እንዲኖረው የተለያዩ አለማቀፋዊ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ወደ ተገባር መግባቱ ይታወቃል ተባለ ፡፡
የኢትዮጲያ ብሄራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የምርመራና ቁጥጥር ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ተስፋዩ ይፍሩ በመዝጊያ ንግግራቸው ወቅት እንደተናገሩት የስፖርተኞች አበረታች ቅመሞች የምርመራና ቁጥጥር ብቃት ያለውና የሰለጠነ ባለሙያ የሚፈልግ ተግባር በመሆኑ ባለን አቅም ላይ ተመስርተን በየደረጃው በውድድር ጊዜም ይሁን ከውድድር ጊዜ ውጭ (In competition and Out of comeptition) በጽ/ቤታችን ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ፡፡ በዚህም ባለሞያዎቹ ወደ ስራ ለመግባት ሙያው የሚጠይቀውን ታላቅ የስነ-ምግባርና ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ጠቁመው ይሄ ስልጠና በአለም አቀፍ ህጎችና ስታንዳርዶች መሰረት በማሰልጠንና Certified በማድረግ ወደ ስራ መግባት የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ባለሞያዎቹ በስልጠናው ላይ በውድድር ጊዜና ከውድድር ጊዜ ውጭ የሚካሄደውን ምርመራና ቁጥጥር በአለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ህግ እና የምርመራና ቁጥጥር ስታንዳርድ መሰረት በአግባቡ ማከናወን የሚያስችላቸውን ግንዛቤና እውቀት በስልጠናው ወቅት ማግኘት መቻላቸውን ገልጿል፡፡
በእለቱም በምርመራ ወቅት ከኮሮና በሽታ ሊደረጉ በሚገቡ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ፡ የስራ የፍቃደ አሰጣጥ በሚመለከት እንዲሁም በላብራቶሪ እና በሪፖርት አደራረግ ወቅት የሚገጥሙን ችግሮች እንዴት መስራት እንዳለባቸው በሚያሳዩ ጉዳዮች ላይ በባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም የስራ ውል ፊርማ ከባለሙያዎች ጋር በመፈራረም እና ለሰልጣኞቸ እውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት የስነ-ስርአት በማካሄድ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡