የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ወጣት ተተኪ አትሌቶችን ከስፖርት ጸረ- አበርታች ቅመሞች ለመጠበቅ የተለያዩ ዕቅዶችን በመቅረጽ እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
(ሐሙስ 09/03/2014 ዓ.ም) የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ በሀይሉ ጀማል እንደተናገሩት ጽ/ቤታችን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ በበጀት አመቱ በዕቅዳችን ትኩረት ሰጥተን ልንሰራባቸው ካሰብናቸው ዋናኛው ጉዳይ በመሆኑ የተተኪ ስፖርተኞችን ግንዛቤ በማሳደግ የችግሩ ተጋላጭ እንዳይሆኑ መጠበቅ ላይ እየስራን ነው ብለዋል ፡፡
በየጊዜው የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመፍጠር የአትሌቶችን አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል ፡፡
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርትና ቢሮ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር ላይ አደርጃጀቶችን በመፍጠር እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የዶፒንግ ከፍተኛ ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ ከአስራ አንዱም ወረዳዎች ለተወጣጡ የስፖርት ባለሙያዎች ፣ የወንዶችና የሴቶች የእግር ኳስ ተጫዋችና አስልጣኞች እንዲሁም የታዳጊ ፕሮጀክት አስልጣኞችና አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ወጣት ማዕከል አዳራሽ ተስጥቷል፡፡
በስልጠናው ከ200 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የህክምና ቡድን ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
ግንዛቤ ማስጨብጫውን የሰጡት የባለስልጣኑ የትምርት፣ስልጠና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈለቀ ዋለልኝ እና የትምህርትና ስልጠና ባልሙያ አቶ ሀብታሙ ካሱ ሲሆኑ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምንነትና መሰረታዊ ጉዳዮች ፣ በሚያስከትለው ጉዳት ፣ በዶፒንግ ህግ ጥሰት ፣ በሰራር ስራዓቶች ዙሪያ እና በሌሎች ገለፃ ተደርጓል ፡፡
በመጨረሻም ከስልጣኞች ጥያቄ እና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *