የአለም አቀፍ ተቋማት የፀረ- ዶፒንግ አመራሮች በ4ኛው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የተጀመረው የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ጠቁመዋል።
በአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) የአፍሪካ የአፍሪካ ሪጅናል ቢሮ ዋና ዳይሬክተር Rodney Swiegelaar እና በአለም አትሌቲክስ የኢንተግሪቲ ዩኒት የምርመራ እና Compliance ኃላፊ Thomas Capdevielle በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጲያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋም ጀምሮ አለማቀፍ ግንኙነቱን በማጠናከር አፍሪካ ውስጥ ካሉ አቻ ተቋማት በተሻለ ሁኔታ ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንደተቻለም ጠቁመዋል። ለዚህም የተቋሙን አመራሮች እና የኢትዮጵያን መንግስት ማመስገን እንደሚገባም ተናግረዋል።
በቀጣይም አገሪቷ የራሷ የሆነ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን መመርመር የሚያስችላት የምርመራ ላብራቶሪ ማቋቋም እንደሚገባት ጠቁመው ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ አመላክተዋል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአለም አቀፍ ደረጃ እየተቋቋመ ባለው የአትሌቶች የፀረ-ዶፒንግ ካውንስል ላይም በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።