የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ Eth-Nado/ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለመፈጸም የሚያስልችል የአቀም ግንባታ ስልጠና ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡
መስከረም 16/2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/Eth-Nado/ በ2014 በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ ለማከናወን ያቀዳቸው ዕቅዶች ውስጥ የጽ/ቤቱን ሠራተኞችን አቅም ማሳደግ አንዱ ነው፡፡ለሰራተኞቹ የሚሰጠው የአወቅም ግንባታ ስልጠና በተከታታይ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን ለወደፊቱም ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡
የስልጠናዉ አስፈላጊነት የጽ/ቤቱ ስራ ባህሪን መሰረት ያደረገ፤ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች በፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣ደንቦችና መሪያዎች፣ በፋይናንስ አሰራርና ሥርዓቶችና መመሪያ ዙሪያ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች በአዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል በመደረኩ ላይ ተገኝተው እደተናገሩት ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በላቀ ደረጃ ለመወጣት አመራሩ እና ሠራተኛው የመንግስት የአሠራር መመሪያዎችን ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ አለበት ብለዋል።
በመሆኑም የዛሬው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አመራሩና ሠራተኛው አዋጆችን፤ መመሪያዎችንና ደንቦችን፣የተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች በመረዳት እና ግልፀኝነት በመያዝ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም በባለቤትነት ስሜት መንቀሳቀስና ለተግባራዊነቱ ሊረባረብ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ስልጠናው ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ ባለሙያዎች፤ በጽ/ቤቱ የትምህርት፣ ስልጠናና ምርምር ዳይሬክቶሬት እና በውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ነው የተሰጠው።
በስልጠና መድረኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ ም/ዋና ዳይሬክተር፣ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *