የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከድሬደዋ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡
ድሬደዋ ከተማ፡(ታህሳስ 13 /2015ዓ፣ም) የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከድሬደዋ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ውይይት አካሄደ ፡፡
በውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋነታዬ ገዛኽኝ ክልሎችና/ከተማ አስተዳደሮች እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያላሳለሰ ጥረት ማድረግ እደሚጠበቅባቸው ተናግረው የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ይህንኑ ለማረገገጥ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አበረታች ቅመሞችን በዘላቂነት ለመከላከል የፀረ-ዶፒንግ ጉዳይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ጀምሮ እዲሰጥ የማድረግ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል፡፡
አበረታች ቅመሞችን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ከግንዛቤ ባለፈ በስራ መዋቅራቸው ውስጥ የፀረ-ዶፒንግ ጉዳይ የሚከታተል ባለሞያ መድበው መስራት እዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ተወካይ በበኩላቸው አበረታች ቅመሞችንወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኮሚሺኑ በትኩረት እደሚሰራ ገልፀው ውይይቱ በቀጣይ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *