የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ እና ንቅናቄ (Social Campaign ) ፕሮግራም በድሬደዋ ከተማ መካሄድ ጀመረ ፡፡
ድሬደዋ ከተማ፡(ታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከድሬደዋ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከታህሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ’’ ንፁህ ስፖርት፤ለዜጎች ተጠቃሚነት’’ በሚል መሪ ቃል የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ እና ንቅናቄ ፕሮግራም በድሬደዋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ ፡፡
የዚህ የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤና ማህበራዊ ንቅናቅ (Social Campaign) ዋና ዓላማ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎችን፤ግንዛቤ ለማጎለብት እና ሲፊ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት እዲሁም የስፖርቱ ማህበረሰብ በቂ ትኩረት እዲሰጥ ለማድረገረግ ነው፡፡
በፕሮግራሙ በስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ መሠራታዊ ጉዳዮችና በሌሎች በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ የተዘጋጁ ብሮሸሮች ተሰራጭተዋል፡፡
በተጨማሪም በተሳታፊዎች መካከል የጥያቄና መልስ፤ እዲሁም ሌሎች ዓይት ውድድሮች ተካሄደዋል ፡፡ ለተሳታፊዎች የተዘጋጁ ቲ-ሸርቶች፣ እስክሪበቶዎች ሽልማት መልክ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ፕሮግራሙ በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዋና ዋና የከተማዋ አደባባዮች በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በሶማሊኛ ቋንቋዎች የመኪና ላይ ቅሰቀሳ እደሚካሄድ በተጨማሪም በከተማው አስተዳደር ስር ለሚገኙ የስፖርት ባለሞያዎች ስልጠና እደሚሰጥ ተግልፃል፡፡
የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራሙ ከፊል ገፅታ በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *