የዶፒንግን ጉዳይ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡
(ህዳር 15/2014 ዓ.ም) የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልል የስፖርት ኮሚሽን የስራ ክፍል አመራሮች በሃዋሳ ከተማ የጋራ ውይይት ዉይይት አካሂዷል ፡፡
የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍሬው አሬራ በዉይይት መድረኩ ወቅት እንደተናገሩት የዶፒንግን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ጉዳዩ ስተራቴጂካል በሆነ መንገድ መመራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የዶፒንግን ጉዳይ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አስታወቋል፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በበኩላቸው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ በአገራችን ስፖርት መሰረታዊ ችግር እንደሆ ገልፀው የኢፌዲሪ መንግስት ይህን በአግባቡ በመገንዘብ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ሲሆን ለዚህም በአገራችን እስካሁን ያለው አፈፃፀምም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ በመሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
በቀጣይም ይህ እንቅስቃሴ በተጠናከረ መንገድ ለማስቀጠል ክልሎች በፎካል ፕረሰን ደረጃ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊውን ሐብት በመመደብና አደረጃጀቶችን እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ በመዘርጋት ዶፒንግን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ስራዎችን መስራት ይገባል ሲሉ በጋራ የውይይት መደረኩ ላይ ገለፀዋል፡፡
በሌላም በኩል ለሐዋሳ ዩንቨርስቲ የ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ድግሪ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች እና መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጥቷል ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *