የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ መርኃ ግብር እንደ ቀጠለ ነው።
በአገራችን ንጹህ ስፖርትን ለማስፋፋትና ጤናማ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት የአትሌቶችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ስራን በተጠናከረ መልኩ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም የምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን ማፍራት አስፈላጊ ሲሆን በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና በተለያዪ ርዕሰ ጉዳዩች እና ባለሙያዎች በንድፈ አሳብና በተግባር የተደገፈ ሙያዊ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡