የፋርማሲ ሴክተሩ በፀረ-ዶፒንግ እንስቃሴው መያዊ ስነ-ምግባርን በመከተል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጥሪ አቀረበ ፡፡
ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀረበው በፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴ ረገድ የፋርማሲ ተቋማት ሚና አስመልክቶ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዝማን ሆቴል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ቦርድ ሰብሳቢ አክሊሉ አዛዥ / ፕሮፌሰር / የስፖርቱ ወረርሽኝ የሆነውን ዶፒንግ በዘላቂነት በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የፋርማሲ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊነት እዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
’’የስፖርት አበረታች ቅመም ወይም ዶፒንግ የአገራችን ስፖርት ዋና ተግዳሮት ከመሆኑ ባለፈ ዜጎቻችንን ለተለያዩ የጤና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግር የሚያጋልጥ ነው ያሉት ቦርድ ሰበሰሳቢው፡፡ ችግሩን በዘላቂነት በመቅረፍ የአገራችንን መልካም ገፅታ ለመገንባትና የዜጎቻችንንም ጤንነት ለመጠበቅ የፋርማሲ ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ እደሆነ’’ ጠቁመዋል ፡፡
’’የስፖርቱን ንፅህናና ደህንነት ለማረጋግጥ ቁልፉ በእናንተ እጅ ነው ያለው፤ስፖርተኞች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለዶፒንግ ህግ ጥሰት እዳይጋለጡ ሞያዊ ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት’’ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የአ.አ ከተማ አሰተዳደር የመድኃኒት፣ምግብና ጤና ክብካቤና ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አመደየሱስ አዳነው እና የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማኀበር ፕሬዝዳንት አቶ ተሰፋዬ ሴፉ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ’’የፋርማሲ ተቋማት ባለቤቶችና አመራሮች በፀረ-ዶፒንግ እንስቃሴው መያዊ ስነ-ምግባርን በመከተል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይርሳል በማጠቃለያ ንግግራቸው የአገራችንን መልካም ገፅታ ለመገንባትና የዜጎቻችንንም ጤንነት ለመጠበቅ የፋርማሲ ባለቤቶችና አመራሮች ሚና ትልቅ ነው ካሉ በኋላ የፋርማ ተቋማት ህጋዊ መስመሩን ብቻ ተከትሎ በመስራት ችግሩን በዘላቂነት በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የድርሻችንን እንወጣ ብለዋል፡፡