የፋርማሲ ባለሞያዎችን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጎልበት የግንዛቤ ማስበጫ መድረክ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ቀን፡- ህዳር 30/2014 ዓ.ም
በስልጠናው መድረኩ ላይ የተገኙት እና የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኢትዮጵያ ፋርማሲ ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ተሰፋዬ ሴፉ የፋርማሲ ሙያ ታማኝ ከሚባሉ የሞያ ዘረፎች አንዱ መሆኑን አሰታወሰው፤ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የዜጎቻችንን ጤንነት አደጋ ላይ ከሚጥልና የአገራችንን መልካም ገፅታ የሚያጠለሹ መሆናቸውን በመረዳት ባለመያዎች የሙያውን ስነ-ምግባር ባከበረ መለኩ ኃላፊነታቸው መወጣት እዳለባቸው አሳሰበዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በአገራችን አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣተር ንፅህ ስፖርት፣ለማስፋፋትና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ በየደረጃው ዘርፈ-ብዙ ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀው፤ሰልጣኞች ከስልጠናው የተሻለ እውቀት በመሸመት ሙያዊ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ የመወጣት ስራ ትሰራላችው ተብሎ ይታመናል በማለት ሰልጣኞች ለስልጠናው ልዩ ትኩረት በመስጠት በንቃት ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸው ከአደራ ጭምር አያይዘው ገልጸዋል፡፡
በማስከተልም ’የስፖርት አበረታች ወይም ዶፒንግ አለም ዓቀፋዊና በሀገራዊ ገፅታና ተፅዕኖ’’ ዶፒንግና የፋርማሲ ባለሞያዎች ሚና ፣በስፖርት የተከለከሉ መድኃኒቶች ዝርዝር ምንነት፣ባህሪና በሚያስከተሉት ጉዳት በሚል ርዕስ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት/ ቤት መምህርና የፋርማሲ ባለሞያዎች ማህበር ተወካይ በሰለሞን አሰፋ /ረዳት ፕሮፌሰር/ ሰፊገለፃና ማብራሪያ ተደርጓል፡፡
በመድረኩ ላይ የፋርማሲ ባለሞያዎችን ጨምሮ የመድኃኒት፣ምግብና ጤና ክብካቤና ባለስልጣን ባለሞያዎች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንደሚጨብጡ ይጠበቃል፡፡
መድረኩ በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን ስፖርተኞች ጉዳት በሚያጋጥማቸው ወቅት የተከለከሉ መዳኃኒቶችን በመጠቀም ተገቢውን ህክምና እዲያገኙ የሚመለከተው የህክምና ፍቃድ አሰጣጥ (TUE)፤ በፀረ-አበረታች ቅመሞች የሕግ ማዕቅፎች እና በፀረ-ዶፒንግ ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ ላይ ገለፀና ውይይት ይደረግበታል፡፡፡