የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ የ2015 ዓ.ም የ6 ወር የስራ አፈጻጻም በመገምገምና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ ።
—————————————————————
በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ከሰራተኞችና አመራሮች ጋር ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ የማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል እንደተናገሩት በ2015 ዓ.ም የስፖርት አበረታች ቅመሞች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ እቅድ በማቀድ ወደስራ የገባን ሲሆን በዚህም የትምህርት ፣ ስልጠና እና የህዝብ ንቅናቄ ፣ ምርመራና ቁጥጥርና የአለም ዓቀፍ ግንኙነትን ማጠናከር እና ሌሎች በዕቅድ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በተቋሙ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰሩ እንደነበር በዝርዝር ተናግረዋል ፡፡
በሌላም በኩል በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ የሚገቡ ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የምርመራና ቁጥጥር ስራችንን ማሳደግ ፣ የህዝብ ንቅናቄና ስልጠና በክለባት እና በክልሎች በስፋት የማዳረስና የግዛቤ አቅምን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየለኩ መሄድ ፣ የኢንተለጀንስና ኢንቨስቲጌሽን ስራን ማጠናከር ፣ የፈጻሚዎችን አቅም ማሳደግ ፣ የህግ ማዕቀፎቻችንን በደንብ ተግባራዊ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፍ ግንኙነቶቻችን በማጠናከር አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተሳትፎዎቻችንን ማሳደግ በቀጣይ ልንሰራባቸው የእንደሚገቡ አመላክተዋል፡፡
አያይዘውም ተቋማችን አዳጊ ተቋም እንደመሆኑ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ተቋሙ የያዛቸው ዕቅዶች ለማሳካት ሰራተኛውና ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚገባ ጠቁመዋል ፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በበኩላቸው ተቋማችንን ለሌሎች ተቋማት ሞዴል ሆኖ መውጣት የሚችልበተን ስራ መስራት ይኖርብናል ለዚህም ሁላችንም በሃላፊነት በመንቀሳቀስ በ6 ወር ውስጥ ፈትሽን ያገኛናቸውን ክፍተቶች በማረም ልንሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡
በጨረሻም ለተቋሙ ሰራተኞች የቢ.ኤስ.ሲ ማስተግበሪያ ሰነድ በአቶ አህመድ ሙሉጌታ አማካኝነት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተደርጎበት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *