የ6ኛ ቀን የዶፒንግ ግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና መርኃ-ግብር
ለአዳማና ዳዲቦሩ አትሌቲክሰ ክለብ አባላት በዶፒንግ ፅን-ሃሳብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡
(ETH-NADO ከሰዓት በኃላ ቅዳሜ ተህሳስ 03/2013 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት”ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ራሳችንን እንጠብቅ” በሚል መሪ ቃል የግማሽ ቀን ከ80 ለሚበልጡ ለአዳማና ዳዲ ቦሩ አትሌቲከስ ክለብ አትሌቶች፤ አመራሮችና ለድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳቦች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ሲሆኑ በንግግራቸውም ላይ በየደረጃው የስልጠና ማዕከላት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያለዉን ግንዛቤ ለማሳደግ በአትሌቶች ሰብዕ እና ባህሪ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ትኩረት ስጥተው ሊሰሩ እደሚገባ አሰገንዝበዋል፡፡
ሥልጠናው በዶፒንግ ጽንስ-ሃሳብ፤ የምርመራ ሂደት፤አሰራር ስራዓት፤የአትሌቶች መብቶችና ገዴታዎች፤በሚስከትላቸው ሁለንታዊ ጉዳቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ ከ80 በላይ የአዳማና ዳዲ ቦሩ አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶች ፤አመራራች፤ አሰልጣኞችና የህከምና ባለመያዎች ተሳትፈዋል፡፡