በአገራችን አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተካሄደ አንቅስቃሴዎችን የሚያሳይ ፎቶ ዓውደ ርይዕ ለእይታ ቀረበ፡፡
(ጥቅምት 5/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ) በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የመሰብሰብያ አዳራሽ በተካሄደው የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በአለፉት አምስት አመታት በአገራችን የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳይ የፎቶ ዓውደ ርዕይ ለእይታ ቀርቦ ታይቷል፡፡
በተጨማሪ በጉባዔው ‹‹የፀረ አበረታች ቅመሞች ረቂቅ ፖሊሲ ››የቀረበ ሲሆነ፣ የጉባኤው ተሳታፊዎች በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ሀሳብ አስተያየት አዲሁም ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በክቡራን ሚኒስቴር ድኤታዎች ምላሽ ተሰጦበታል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *