የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን/ ETH ADA/ በኦሮሚያ ክልል የጂማ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ለማርሻል አርትስና ለጅምና ስቲክስ ክለብ ታዳጊ አትሌቶችና አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሚያዚያ 05 ቀን 2014 ዓ.ም በዞኑ ባህልና ስፖርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ተሰጠ፡፡
በመድረኩ ላይ 50 የሚሆኑ አትሌቶችና አስልጣኞች ስልጠናዉን ተከታትለዉታል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን /ETH ADA/
አበረታች ቅመሞች በአትሌቶች ላይ የሚያስከትለዉን የጤና፣ የስነ ልቦና ኢኮኖሚያዊ ተፅኖ ለመከላከልና የታዳጊ ስፖርተኞችን ግንዛቤ ለማጎልበት በአዲሱ ሥራተ ትምህርት ሮድማፕ ውስጥ ከአምስተኛ ከፍል ጀምሮ በመደበኛ የትምህርት ካሪኩለም በስምንት የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ተካቶ ተግባራዊ ለማድረግ ትከረት ተሰጠቶ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ገልፀው ፣ የመማሪያ መፅሐፍት ህትመት ሥራው እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጯ ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች እደተናገሩት በተለይ በጅማ ዞን የሚገኙ ታዳጊ ስፖርተኞች በግንዛቤ እጦት የተነሳ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ንጠረ ነገሮችን (supplements) ያለአግባባብ የመጠቀም ዝንባሌ እዳለ ተናግረዋል፡፡ ድጋፍ ሰጭ ንጠረ-ነገሮች (supplements) ለዶፒንግ ህግ ጥሰት ተጋላጭነት በተጨማሪ የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ መሆናቸውን ግንዛቤ እዳስጨበጧጨው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ተሳታፊው በተሰጠው ትምህርት ላይ ምንያህል ግንዛቤ እደጨበጡ ለማረጋጥ የጥያቄና መልስ በስልጠና ባለሞያው በአቶ አብታሙ ካሱ ቀርቦ ለተሳታፊዎች የተለያዩ ሽላማቶች ተበረክጽዋል ፡፡

By Ermias