ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡
ግንቦት 20/2013 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/ አዘጋጅነት የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች በዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር እና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ በአዳማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ፡፡
በመድረኩ 55 የሚሆኑ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎች /Chaperones , DCOs and BCOs / ተሳትፈዋል ።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና በ2021 የተከለሰው የምርመራ ባለሙያዎች መመሪያ ሰነድ ፣ የምርመራ ባለሙያዎች የደረጃ እድገትና የስራ ስምሪት ፣ በምርመራና ቁጥጥር ስራዎች ላይ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ዙሪያ እንዲሁም የጽ/ቤቱ የ10 ወር የስራ አፈጻጸም በባለሙያዎች ቀርበው ውይይት፣ የሚደረግባቸው ይሆናል ።