ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለአርባ ምንጭ ሴቶች ፕሪምር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ሐዋሳ ከተማ፡ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የሚሰጠውን ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡የስልጠናው ዋነኛ ትኩረት በቀጣይ አትሌቶች አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ በመከላከል ረገድ ሊያውቋቸውና ተግባራዊ ሊያደርጓቸው በሚገቡ ጉዳየች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
እንጀራዬ፣ህይወቴ ስፖርት ነው ካላችው በቅድሚያ ራሳችን ከአበረታች ቅመሞች/ዶፒንግ ማራቅ አለበን ፡፡ታዋቂና ዝነኛ መሆን ብቻውን በቂ አይደለም፣ ከአበረታች ቅመሞች እራሳችን እሳካልጠበቅን ድረስ የልፋታችን፣ የድካማች ውጤቱ መጨረሻው የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው ስለሆንም አትሌቶች አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ የሚያስከትለውን ተፅኖ እና የአሰራር ስርዓቱን ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ እዳለባቸው የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ስልጠናውን አስመልክተው በአስተላለፉት መልዕክት ላይ ገልፀዋል ፡፡
በመጨረሻም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና ክለቦች ስፖርተኞቻቸውን ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ሊጠብቁ እንደሚገባ ም/ዋና ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡
በስልጠና መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባ ምንጭ ሴቶች ፕሪምር ሊግ ተሳታፊ ክለብ አትሌቶችና የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች (የስነ-ምግብ፣ የህክምና ባለሞያዎች፣ ወጌሻዎች) ተሳታፊ ሆነዋል፡፡