የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌድሬሽን ለእግር ኳስ ክለብ አሰልጣኞች የፀረ -ዶፒንግ የሙያ ፍቃድ (license) መስጠት እዲሚጀምር ተጠቆመ፡፡
ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምር ሊግ እግር ኳስ ክለቦች በስፖርት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የሚሰጠው ሥልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለቅዱስ ጎርጊስ እና ለልደታ ክ/ከተማ ሴቶች እግርኳስ ክለብ ስልጠና ተሰጥቷል
ሐዋሳ ከተማ፣ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በትብብር በተዘጋጀው የሴቶች እግርኳስ ክለቦች የስልጠና መድረኩ ላይ የተጉኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የህክምና ባለሞያ ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ እደተናገሩት የኢትዮጵያ የእግርኳስ ፌድሬሽን አበረታች ቅመሞችን /ዶፒንግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከባለስልጣኑ ጋር በትብብር እየሰራን ነው፤ለእግር ኳስ ክለብ አሰልጣኞች የፀረ-ዶፒንግ የሙያ ፍቃድ(license) መስጠት እደሚጀመር ጠቁመው፤ይህም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይዶ/ር ሳሙዔል ባስተላለፉት መልዕክት አትሌቶች በሚመገቡት፣ ለህክምና የሚውስዱት መደሃኒቶች ላይ ጥንነቃቄ ማድረግ አለባችው፤ በተለይ በፋብሪካ ምርት የሆኑ የታሸጉ ምግቦችና የህክምና መዳሃኒቶች ላይ እረግጠኛ መሆን ስለማይቻል የግድ የባለሞያ ምክር ይፈልጋ ፤አትሌቶች እራሳችውን ከአበረታች ቅመሞች ልትጠብቁ ይገባል በዚህ ረገድ የስፖርት ባለሞያዎች ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በሥልጠናው መክፈቻ ላይ መልዕክት በማስተላለፍ መድረኩን ሲያስጀምሩ እዳሉት ስፖርት ሥራችን፣ህይወታችን ነው፡፡ ካላችው እራሳችሁን ከአበረታች ቅመሞች/ዶፒንግን መጠበቅ ግድ ይላል ብለዋል፡፡ዶፒንግ አትሌቶችን በስፖርት ውስጥ ያላቸውን የስራ ቆይታ ከማሳጠር ባለፈ ለወንጅል ቅጣት የሚዳርግ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምር ሊግ እግርኳስ ክለቦች በሐዋሳ ከተማ በአበረታች ቅመሞች/ዶፒንግ ላይ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለቅዱስ ጎርጊስ እና ለልደታ ክ/ከተማ ሴቶች እግርኳስ ክለብ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በአበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮችና ተያየዥ አጀንዳዎች ላይ ያተኩረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *